Skip to main content

የስፖርት ስልጠናና የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ልማት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት 

የክልላችን መንግስት በስፖርት ልማት ላይ ከስቀመጠቸው ግቦች ውስጥ፤ ትልቁን ድርሻ የያዘው የክልሉን ተተኪ ስፖርተኞችን ችግር በመቅረፍ በክልል፣ በሀገራ አቀፍ እና በዓለማ አቀፍ የስፖርት ውድድር መድረኮች፤ የክልሉንንና የአገራችንን ክብርና ዝና ማስጠበቅ የሚችሉ ስፖርተኞችን በሁሉም ዘርፍ ለማፍራት የሚረዳ፤ የስፖርት ልማት ግብ መሠረት ባደረገ መልኩ በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ፖቴንሽያልን መሠረት በማድረግ ፤ በሁሉም በዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ፕሮግራም ተዘርግቶ፤ በመተግበር ላይ ይገኛል። 

ይህ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ፕሮግራም ፤ ከተጀመረበት ብዙ ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም፤ የስልጠና አሰጣጥ ሂደትን ለማሳከት ዋናው ዘዴ የምዘና ወድድር በመሆኑ፤ የስልጠናውን አሰጣጥ ደረጃ እና ውጤት ያለበትን ሁኔታ መለከት አስፈላጊ ስለሆነ የተያዩ የዉድድር መድረክ እያዘጋጀ ይገኛል። የኢትዮጵያ ስፖርት ፖሊስ ዓለማው፤ ከአጠቃላይ የህብረተሰብ እንቅስቃሴ በመነሳት በተለይም፤ የወጣቱን የስፖርት ልማት ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፤ የትውልድን ግንዛቤና ተሳትፎ በማጠናከር የላቀ ችሎታ ያላቸውን ምርጥ ስፖርተኞችን በማፍራት፤ በክልል፣በሀገር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡና፤ የክልላችንንና የሀገራችንን ስም የሚያስጠሩ ታዳጊና ተተኪ ምርጥ ስፖርተኞችን ለማፍራት እየሰራ ይገኛል።