የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ወጣቶች በሀገራችንና በክልላችን በሚካሄደው ልማት ንቁ ተሳታፊና ከሚገኘው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድገት እኩል ተጠቃሚ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ጤናማና አምራች ዜጋን ለመፍጠር በተሰማራበት የሙያ ዘርፍ ምርታማነትን ለማሳደግ፣ እንዲሁም ስፖርት በኢኮኖሚ ልማት ግንባታ ሂደት ውስጥ የሚኖረውን ሚና እንዲወጣ ለማድረግ እና ከህብረተሰብ ተሳትፎ በመነሳት በመልካም ስብዕና የታነፁ ወጣቶችንና ምርጥ ስፖርተኞችን ለማፍራት በሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ውድድር መድረክ ተሳታፊ፣ ተፎካካሪ፣ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በክልሉ ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 195/2015 የተቋቋመ ሲሆን፤ ቢሮዉ በክልሉ በወጣቶችና በስፖርት ዙሪያ የምሰጡትን አገልግሎቶችና ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚከናወኑ ተግባራትን የሚፈፅምበትና የሚያስፈፅምበት ስልጠንና ኃላፊነት ተሰጥቶት ተቋቁሟል፡፡