AdminYouthsport
በዓለም ሚሊተሪ አገር አቋራጭ ውድድር የመቻል አትሌቲክስ ቡድን የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሆነ። የካቲት 23፣ 2018ዓ.ም (ዱራሜ) በግሪክ ትሪካላ ከተማ 38 ሀገራት በተሳተፉበት 60ኛው የዓለም ሚሊተሪ አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ውድድር ሀገራችንን በመወከል ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መቻል ስፖርት ክለብ በድብልቅ ሪሌ አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሆነዋል።
በድብልቅ ሪሌ ተሳታፊ በመሆን ለሀገራችን የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ያስገኙት አምሳ አለቃ ደጀኔ ተሾመ፣ አስር አለቃ ዮብሰን ብሩ መሠረታዊ ወታደር መሠረት ሙሉጌታ እና መሠረታዊ ወታደር ጫልቱ ታደሰ ናቸው።