Skip to main content
youthnews5

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለምአቀፍ ውድድር ልታዘጋጅ ነው። ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለምአቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር እንድታዘጋጅ የዓለም አትሌቲክስ እድል ሰጥቷታል። የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን በያዝነው ወር መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያ የሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የስፖርት ዲፕሎማሲን ለማጠናከር እና በትብብር ለመስራት ከስፖርት ዘርፍ ሀላፊ ጋር ሰፊ ውይይት መደረጉ የሚታወስ ነው።

ዋና ዳይሬክተሩ በጉብኝታቸው "ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውደድሮችን ለማዘጋጀት አቅም እንዳላትና፣ የተለያዩ ውድድሮችን ወደ ኢትዮጵያ እናስመጣለን ማለታቸው" የሚታወስ ነው።