AdminYouthsport
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ዘርፍ የልዩ ልዩ ሻምፒዮ እና የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል ማጠቃለያ ሪፖርት ተገመገመ።
ዱራሜ፣ የካቲት 30/2018 ዓ ም) በክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት በጉራጌ ዞን አስተናጋጅነት በወልቂጤ ከተማ ለአስር ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የሰነበተው 3ኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልዩ ልዩ ሻምፒዮና፣ እና የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል አጠቃላይ ህዳቱ ውጤታማ እና ለቀጣይ ልምድ የተወሰደበት እንደሆነ የቢሮ ም/ሃላፊና ስፖርት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሰይፈ አለሙ ገልፀዋል።
በመድረኩም ሁሉም ንዑሳን ኮሚቴዎች ሪፖርቶቻቸውን አቅርበዉ አስገምግመዋል። ሪፖርቱን የገመገሙት የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰይፈ አለሙ እንደተናገሩት ውድድርና ፌስቲቫሉ ፊጹም ሰላማዊ እና ስፖርታዊ ጨዋነት የታየበት ነበረ ። ውድድሩም ወንድማማችነት እና እህታማማችንት ጎልቶ የታየበት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሰይፈ፣ ይህን ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በማስቀጠል ለቀጣይ ውድድሮች ልምድ የተወሰደበት እንደሆነም አመላክተዋል።