AdminYouthsport
ፎቴን ተስፋይ ሁለተኛውን የማራቶን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸነፈች። መጋቢት 06፣ 2018ዓ.ም ዱራሜ በስፔን በተካሄደ የነሐስ ደረጃ ባለው የባርሴሎና ማራቶን አትሌት ፎቴን ተስፋይ በታሪክ ሁለተኛውን የዓለም ፈጣን ስዓት በማስመዝገብ አሸንፋለች። አትሌት ፎቴን 2:10:53 በሆነ ሰአት ቀዳሚ ሆና በመጨረስ፣ የቦታውን ክብረወሰን በመስበር ጭምር ነው ድል ያደረገችው። ፎቴን ተስፋይ በመጀመሪያ የማራቶን ውድድሯ ነው አዲስ ታሪክ በማስመዝገብ ለድል የበቃችው። በውድድሩ ዘይነባ ይመር፣ ጫልቱ ጬምዴሳ እና ያልጋነሽ ገደፋ ከሶስት እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። በወንዶች ኡጋንዳዊው አቤል ቼላንጋት በአንደኝነት አጠናቋል። #ባህልና ስፖርት ሚንስትር